በምስራቅ ሀረርጌ የባሏን ገዳይ በምህረት ከእስር በመውጣቱ ምክንያት ከቤተሰቦቿ ጋር በመተባበር ያስገደለችው ግለሰብ እና ግብረ አበሮቿ በጽኑ እስራት ተቀጡ
በ2014 ዓ.ም ያዩ ሀሰን እና አልዩ ሀሰን የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች (የአይሻ አጎት ልጆች) የአይሻን ባለቤት በስለት ወግተው ገድለውት ነበር። በወቅቱ በነበረው የፍርድ ሂደት ያዩ ሀሰን ጥፋተኛ ተብሎ ሲታሰር፣ ወንድሙ አልዩ ሀሰን ግን በነጻ ተለቆ ነበር።
ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ቀዳሚው ገዳይ ያዩ ሀሰን በምህረት ከእስር ይፈታል። በዚህ የተበሳጨችው የሟች ሚስት አይሻ አህመድ፣ ከቤተሰቦቿ (አህመድ እዩ፣ አፈንዲ ጀማል እና መሃመድ አልዩ) ጋር በመሆን ሴራ ጎነጎነች።
ግለሰቦቹ እንደ ገጀራ እና ሜንጫ ያሉ ስለታም መሳሪያዎችን በመያዝ፣ ከእስር የተፈታውን ያዩ ሀሰንን እና ቀድሞ በነጻ ተለቆ የነበረውን ወንድሙን አልዩ ሀሰንን በመደብደብ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አህመድ አዪ እና አፈንዲ ጀማልን
በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣አይሻ አህመድ (አስተባባሪ) እና መሀመድ አልዩን እያንዳንዳቸው በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጥቷል።

9 months ago