ለጤናማ ህይወት በቀን ስንት ሰዓት መተኛት አለብን?
ብዙዎቻችን "ጥሩ እንቅልፍ" ስንል ለሁሉም ሰው እኩል የሆነ ሰዓት ይመስለናል፤ ነገር ግን የእንቅልፍ ፍላጎት እንደ እድሜ እና እንደ ጤና ሁኔታ ይለያያል።
እንደ እድሜ ክልል የሚመከሩ የእንቅልፍ ሰዓታት፦
አዲስ የተወለዱ ህፃናት፦ በቀን ከ14 እስከ 17 ሰዓት
ተማሪዎች (ህፃናት)፦ በቀን ከ9 እስከ 12 ሰዓት
አፍላ ወጣቶች (Teenagers)፦ በቀን ከ8 እስከ 10 ሰዓት
አዋቂዎች፦ በቀን 7 እና ከዚያ በላይ ሰዓት
ጥቂት መተኛት ምን ጉዳት አለው?
አንድ አዋቂ ሰው በቀን ከ7 ሰዓት በታች አዘውትሮ የሚተኛ ከሆነ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ሊጋለጥ ይችላል። ከነዚህም መካከል፦
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉የስኳር በሽታ
👉የደም ግፊት እና የልብ ህመም
👉የአእምሮ ጭንቀት (Depression)
በእንቅልፍ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮች፦
የእንቅልፍ ጥራት፦ እንቅልፍዎ የሚቆራረጥ ከሆነ ለረጅም ሰዓት ቢተኙም ሰውነትዎ አያርፍም።
የእንቅልፍ እዳ፦ ከዚህ ቀደም በቂ እንቅልፍ አጥተው ከሆነ፣ ሰውነትዎ ለማገገም ተጨማሪ ሰዓት ሊፈልግ ይችላል።
ነፍሰ ጡር፦ የሆርሞን ለውጥ እና አካላዊ ምቾት ማጣት ተጨማሪ እረፍት ያስፈልጋቸዋል።
እድሜ፦ አረጋውያን ልክ እንደ ወጣቶች ተመሳሳይ ሰዓት ቢፈልጉም፣ እንቅልፋቸው የመቅለል እና የመቆራረጥ ባህሪ ይኖረዋል።
ጥሩ እንቅልፍ ለልጆች የተሻለ ትኩረትና የማስታወስ ችሎታን ሲሰጥ፣ ለአዋቂዎች ደግሞ በሽታን የመከላከል አቅምን ያጠናክራል።

7 months ago