Logo
FIDEL POST NEWS
​🌑 በ86 አመታቸው የሞቱት ባባ ቫንጋ አዲሱ የፈረንጆቹን አመት የዓለም ጦርነት እና የባዕድ ፍጥረታትን ይከሰትበታል ብለው ተንብየዋል

​"የባልካን ኖስትራዳመስ" በመባል የሚታወቁትና በርካታ ዓለም አቀፍ ክስተቶችን አስቀድሚ በመተንበይ የሚታወቁት ቡልጋሪያዊቷ ባባ ቫንጋ ይህ የፈረንጆቹ 2026 እጅግ አስፈሪ ትንቢቶችን አስቀምጠዋል

​የትንቢቱ ዝርዝር ነጥቦች፦
​🚀 የባዕድ ፍጥረታት ጉብኝት፦ እንደ ቫንጋ ትንቢት ከሆነ፣ የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባዕድ ፍጥረታት (Aliens) ጋር በህዳር 2026 ይገናኛል። ግዙፍ የሆነ የባዕድ ፍጥረታት መንኮራኩር ወደ ምድር ከባቢ አየር እንደሚገባ ብትተነብይም፣ የመጡበትን ዓላማ ግን አልገለፁም።

​⚔️ የሦስተኛው ዓለም ጦርነት፦ ከሁሉም አስፈሪው ትንቢታቸው በ2026 የሦስተኛው ዓለም ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ያስጠነቀቁበት ነው። ይሁን እንጂ ቫንጋ የዓለም ፍጻሜ እስከ 5079 ዓ.ም ድረስ እንደማይሆን ገልፀዋል። ይህም ማለት ጦርነቱ የሰው ልጅ የመጨረሻ ምዕራፍ አይሆንም ማለት ነው።

​⚠️ የሞራል እና የቴክኖሎጂ ውድቀት፦ የሰው ልጅ በቴክኖሎጂ እና በሥነ-ምግባር ረገድ "ከመጠን በላይ ርቆ የሄደበት" ወሳኝ ነጥብ ላይ መድረሱን እና ወደ ማይመለስበት ጥፋት እየተቃረበ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።

​ለምን ትኩረት ሳበ?
በቅርቡ በጠፈር ላይ የሚታዩ ያልታወቁ የሚበሩ አካላት (UAPs) መብዛት እና በፀሐይ ስርአት ውስጥ የታየው "3I/ATLAS" የተሰኘው እንግዳ አካል በሳይንቲስቶች ዘንድ መነጋገሪያ መሆኑ የቫንጋን ትንቢት ለብዙዎች አሳማኝ አድርጎታል።

​🔮 የእርስዎ አስተያየት ምንድነው? እነዚህ ትንቢቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ ብለው ያስባሉ ወይስ እንዲሁ ግምቶች ናቸው?
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.