ማስክ የአንጎል ውስጥ መትከያዎችን በብዛት ማምረት ጀመረ
ቺፑ ተጠቃሚዎች በአእምሮአቸው ኃይል ብቻ የጠፉ የአካል ክፍሎችን ተግባራት እንዲመልሱ ያስችላቸዋል
የኢለን ማስክ ኩባንያ የሆነው ኒውራሊንክ በዚህ አመት የአንጎል ውስጥ መትከያ መሣሪያውን በከፍተኛ ደረጃ ማምረት እንደሚጀምር ማስክ በኤክስ (X) ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ ገልጿል።
የኒውራሊንክ መትከያ ከአንጎል የሚመነጩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን በማንበብና ወደ ዲጂታል ትዕዛዞች በመቀየር አንጎልን ከኮምፒውተር ጋር ለማገናኘት የተነደፈ ነው።
ዋና ዓላማውም ተጠቃሚዎች የተለያዩ መሣሪያዎችን እንዲቆጣጠሩ ወይም በአእምሮአቸው ኃይል ብቻ የጠፉ የአካል ክፍሎችን ተግባራት እንዲመልሱ ማስቻል ነው።
በኒውራሊንክ ድረ-ገጽ ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው፣ የአንጎል ሴሎችን መረጃ ለመተርጎም ኤሌክትሮዶች በአንጎል ውስጥ በሚገኙ የነርቭ ሴሎች አቅራቢያ ይቀመጣሉ።
ድረ-ገጹ አክሎም “ለምሳሌ ያህል፣ ከእንቅስቃሴ ጋር በተያያዙ የአንጎል ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ የነርቭ ሴሎች የታቀዱ እንቅስቃሴዎችን ይወክላሉ። በአንጎላችን ውስጥ ስለምናየው፣ ስለሚሰማን፣ ስለምንነካው ወይም ስለምናስበው ነገር ሁሉ መረጃ የሚሸከሙ የነርቭ ሴሎች አሉ” ይላል።
ይህ ቺፕ ሙሉ በሙሉ በአንጎል ውስጥ የሚቀበርና ከውጭ የማይታይ ሲሆን፣ ውፍረቱም 1.75 ኢንች ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
ኩባንያው በምግብና መድኃኒት አስተዳደር (FDA) በኩል የቀረቡለትን የደህንነት ስጋቶች መፍትሄ ከሰጠ በኋላ፣ በ2024 በሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ ጀምሯል። መጀመሪያ በ2022 ያቀረበው ማመልከቻ ውድቅ ተደርጎበት እንደነበር ይታወሳል።

9 months ago