ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ማርሸት ዘውዱ ለ2025 የአፍሪካ ምርጥ የቴኳንዶ ዳኛነት ሽልማት ታጨች
#ethiopia | በቴኳንዶ ስፖርት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ በብቃት ስታገለግል የቆየችው ማስተር ማርሸት ዘውዱ፣ ለ2025 የአፍሪካ የቴኳንዶ ምርጥ ዳኛ (Best African Referee) ሽልማት እጩ መሆኗ ተገለጸ።
ማርሸት ዘውዱ በስፖርቱ ዘርፍ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ያደረገች ባለሙያ ስትሆን፤ በብሔራዊ ቡድን ተጫዋችነት ሀገሯን ወክላ ሜዳሊያዎችን ከማጥለቋም ባሻገር፣ በብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝነት በርካታ ታዳጊዎችን በማብቃት ሀገራዊ ግዴታዋን ተወጥታለች።
በዳኝነት ሙያዋም በተለይም በ2025 የውድድር ዓመት በማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኮትዲቫር እና ኢትዮጵያ የተካሄዱ ታላላቅ አህጉራዊ ውድድሮችን በብቃት በመምራት ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን አግኝታለች።
በአሁኑ ወቅትም ለዚህ ክብር ከናይጄሪያ፣ ከግብፅ እና ከኮትዲቫር አቻዎቿ ጋር ለሽልማት የቀረበች ሲሆን፣ አሸናፊውን ለመለየት የህዝብ ድምፅ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
ምርጫው ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜ ሦስት ቀናት ብቻ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ለሀገራቸው ልጅ ድምፅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
ድምፅ ለመስጠት፡
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ከስሟ (Marshet Zewdu) ፊት ለፊት የሚገኘውን ክብ ምልክት መምረጥ ብቻ በቂ ነው።
የድምፅ መስጫ ሊንክ:
https://www.facebook.com/s...

9 months ago