ቻይናውያን የቀዶ ጥገና ሐኪሞች የተቆረጠውን የታካሚ ጆሮ በእግሯ ላይ በመትከል ሕይወቷን አተረፉ
የቻይና መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ባለፈው ሚያዝያ ወር በሥራ ቦታ ባጋጠማት አደጋ የሴቲቱ ጆሮ የተቆረጠ ሲሆን፣ አብዛኛው የራስ ቅሏ ቆዳም ተገሽልጦ ነበር። የሻንዶንግ ሆስፒታል ጥቃቅን ቀዶ ጥገና ክፍል፣ በእግር ላይ ያሉ የደም ሥሮች ለጆሮው ተስማሚ የሆነ ውፍረት ስላላቸው ጆሮውን በእግሯ ላይ ተክለውት ቆይተዋል።
ለአምስት ወራት ያህል፣ ከሆዷ ላይ በተወሰደ ቆዳ አማካኝነት የራስ ቅሏ እና የአንገቷ ቁስል እንዲድን ተደርጓል። በሰባተኛው ወር መጨረሻ ላይ ደግሞ በእግሯ ላይ የቆየው ጆሮዋ ተነቅሎ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ ተደርጓል።

10 months ago