Logo
SeledaPost
በፈጣሪ ቸርነት የተረፈው ታዳጊና አደገኛው ጉዞ!

ከደምቢደሎ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ስር ተደብቆ፣ ከ600 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው የ10 ዓመት ታዳጊ በሰላም ተገኘ።

ታዳጊው ጉዞውን የጀመረው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ደምቢደሎ ላይ ሲሆን፣ ማንም ሳይመለከተው በአውቶብሱ ስር ያሉ የብረት ክፍሎችን ሙጥኝ ብሎ በመያዝ ለሰዓታት አደገኛ ጉዞ አድርጓል። ታዳጊው ይህንን ሁሉ ርቀት (645 ኪሎ ሜትር) ያለምንም ጉዳት መጓዙን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አውቶብሱ ሆለታ አካባቢ ሲደርስ፣ ከታችኛው ክፍል የሚወጣ እንግዳ ድምፅ የሰሙ ተሳፋሪዎች ለሾፌሩ ጥቆማ ይሰጣሉ። መኪናው ቆሞ በተደረገ ፍተሻም፣ ታዳጊው ከአውቶብሱ ስር በህይወት ተገኝቷል።

ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በአስኮ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች ማንኛውንም ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የመኪናቸውን ደህንነትና ስር መፈተሽ እንዳለባቸው ትልቅ ትምህርት የተሰጠበት ሆኗል።

"ታዳጊው በጉዞው ላይ ጉዳት ደርሶበት ቢሆን ኖሮ ሾፌሩ ለከባድ የህግ ተጠያቂነት ይዳረግ ነበር፤ በመሆኑም ቅድመ ጥንቃቄ ወሳኝ ነው" ሲሉ ጉዳዩን የተከታተሉ አካላት ገልጸዋል።

Via የሹፌሮች አንደበት

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.