እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በይፋ መስጠቷን አስታወቀች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር በይፋ መቀበሉን አስታወቁ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ መሆኑ ተገልጿል።
ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዕውቅናው የተረጋገጠው ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እና ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በጋራ በተፈረመ "የሁለትዮሽ ስምምነት" አማካኝነት ነው።
ጠ/ሚሩ በመግለጫቸው ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመውን "የአብርሃም ስምምነት" መንፈስን የተከተለ መሆኑን ገልፀዋል።
ነታንያሁ ፕሬዝዳንት አብዲራህማንን "ታሪካዊ መግለጫ" ባሉት በዚህ ስምምነት ላይ እንኳን ደስ ያለዎት ያሏቸው ሲሆን፤ ለሰላም እና ለመረጋጋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና አመራር ምስጋና አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።
እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን በወሰዱት እርምጃ ደስታቸውን ገልጸው፤ እስራኤል ሽብርተኝነትን በመዋጋትና ቀጣናዊ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለምትጫወተው ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሂደት መሳካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፣ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የእስራኤል የደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።
ነታንያሁ እንደገለጹት፤ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በሚደረጉ ሰፊ ትብብሮች አማካኝነት ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
Via አዲስ ስታንዳርድ

10 months ago