Logo
Getu Temesgen
ረጅም ሰዓት መቀመጥ ሲጋራ ከማጨስ አይተናነስም ሲባል ሰምተዋል ?
#ethiopia | ይህ አገላለጽ ሳይንቀሳቀሱ ለረጅም ሰዓታት መቀመጥ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከሲጋራ ማጨስ ጋር እኩል አደገኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ሰዎችን ለማንቃት እያገለገለ ይገኛል።

በሥራ ምክንያት ሆነ በሌላ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ ይህ አገላለጽ በእውነትም ሊያስጨንቆት ይገባል።

በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ረጅም ሰዓት መቀመጥን በዋናነት የሚያስከትሉትን የጤና አደጋዎች እንዲህ ይገልጹታል፦

- ለረጅም ሰዓት መቀመጥ የሰውነትን ስብ የማቃጠል አቅም በ90% ይቀንሳል።

- የደም ግፊትን ይጨምራል።

- ከመጠን ላለፈ ውፍረት በማጋለጥ ለስኳር፣ ለልብ ህመም እና ለተለያዩ የካንሰር ዓይነት በሽታዎች ያጋልጣል።

- በቀን ከ6 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ሰዎች፣ ከ3 ሰዓት በታች ከሚቀመጡት ጋር ሲነፃፀሩ በ15 ዓመት ውስጥ የመሞት እድላቸው በ40% ከፍ ያለ ነው።

- ንቁ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለጭንቀትና ለድብርት (Depression) ተጋላጭነትን ይጨምራል።

ይህን ያህል ረጅም ሰዓት መቀመጥ አደጋ ከሆነ ምን እናድርግ ?

ልክ ሲጋራን ማቆም ለጤና ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ፣ ለረጅም ሰዓት ያለ እንቅስቃሴ የመቀመጥ ዝንባሌያችንን ማስቀረት የህልውና ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።

ለዚህም የሚከተሉት እርምጃዎች እንደ መፍትሄ መቀመጥ ይችላሉ፦

- ከተቻለ በ30 ደቂቃው ከወንበር ተነስቶ ለጥቂት ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ማድረግ፤

- በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ፈጣን እርምጃ ወይም ስፖርት ማዘውተር፤

- ስልክ ሲደወልልዎት ወንበርዎ ላይ ከመቀመጥ ይልቅ እየተንቀሳቀሱ ማውራት፤

- በሊፍት ፋንታ ደረጃን መጠቀም የደም ዝውውርን ማሻሻል፤

በአጠቃላይ ወንበር ላይ ረጅም ጊዜን ማሳለፍ ልክ እንደ ሲጋራ ጢስ ቀስ በቀስ ጤናን የሚያውክ በመሆኑ፣ መንቀሳቀስ ለጤናችን ግድ መሆኑን አውቀን በጊዜ እንዘይድበት መልዕክታችን ነው።
#tm

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.