Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ የስልጣኔና የአይበገሬነት ምሳሌ ናት !
የህንዷ ጋዜጠኛ ፓልኪ ሻርማ On Firstpost

መቼም ከሰሞኑ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ መጥተዉ እንደነበር ሰምታችኋል ።

ጉብኝታቸው ተከትሎ የሀገራችን ሚዲያው ብዙ ስላሉ ደግሜ አላሰለቻችሁም ።

ልነግራችሁ የፈለኩት ዘመን ባመጣዉ የሰፈር አጥር የታጠርን የዚህ ዘመን ዜጎቿ እኛ ኢትዮጵያዊያን እንኳን በዚህ ሁኔታ ሀገራችን በማንገልፅበት እዉነታ የጋዜጠኛዋና ስለኢትዮጵያ አብጠርጥራ መረጃዎች በማዘጋጀት ዜናዉን የዘገበችበትን መንገድ ስለገረመኝ ላጫዉታችሁ ነዉ ።

ያዉ የሀገራችን ሚዲዎች የህንዱ ፕሬዘዳንት ኢትዮጵያ መጥቶ በሚል በሰጡት ሽፋን እንደስኬትና ትልቅ ድል በማድረግ ብዙ ብለዋልና ልለፈዉና ።

በእኛ ወገን እንደተዘገበው ሁሉ በህንዱ ተወዳጅ ጣቢያ Firstpost ዘገባ ላይ ልረፍ ።

ይህን ዜና የሰራችው ፓልኪ ሻርማ የህንድ በጣም ተወዳጅ ጋዜጠኛ ስትሆን ለታሪክ ቅርሶች እና ባህል ላይ የተመሰረቱ እሴቶች በማስቀጠል ሙያዋን ትገለገልበታለች አለምአቀፋዊ ጥልቅ ትንተናዎቿ መሳጭ ናቸዉ ።
እንዲያውም አንዳንዴ ዘገባዎቿን ስሰማቸዉ ቀላልና ማራኪ በመሆናቸዉ አማርኛ የምትናገር ነዉ የሚመስለዉ ። ልምድ ችሎታዋ ልዩ ተቀቃይነት ያስገኘላት ሲሆን ህንዳዉያን ጋዜጠኛዋን ከታዋቂዎቹ የዲሞክራሲ ምሰሶዎች አንዷና የ ጋዜጠኝነት ችቦ እስከማለት ደርሰዋል ።

የምትሰራበት ጣቢያ ህንድ ነዉና መቀመጫዉ በእለቱ በምሽት የዜና እወጃ አንከር የነበረችዉ ጋዜጠኛዋ የህንዱ ፕሬዘዳንት ለጉብኝት ኢትዮጵያ ናቸዉ የሚል ዘገባውን ጀመረች ። ዜናው የተለመደው አሰልች የሆነዉን ካልሆነዉ የቀላቀለ ፕሮፖጋንዳ የበዛበት ፖለቲካ ብቻ አልነበረም ። ጥቂት ስለ ጉብኝቱ እንዳወራች ድንገት ሀሳቡን ገታ በማድረግ የድምጿን ቃና ቀየር አድርጋ ።

ይልቅ ስለኢትዮጵያ ልንገራችሁ ስትል ጀመረች ። ቀጠለች ከመጀመርያዉ እንጀምር ለዛሬው ምሽት የኢትዮጵያን ታሪክ ልንገራችሁ ።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ስትሆን ዋና ከተማዋ አዲስአበባ ትባላለች ።

የኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ጥንታዊና አስደናቂ ነዉ ።የአለም ቀደምት ስልጣን መነሻ ናት ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የሰዉ ልጅ ፍጥረታት ለመጀመርያ ጊዜ ይኖሩባት የነበረች የሰዉ ዘር መገኛ ናት ።

ከአህጉሪቱ ብቸኛ በቀኝ ያልተገዛች በነፃነት የኖረች ስትሆን የአፍሪካ መሰብሰቢያ ዋና ማዕከልም ናት ። የብሪክስ አባልም ናት ።

ብዙ ሰዉ አያዉቀዉም ኢትዮጵያና ህንድ ወዳጅነት የተጀመረው ከሁለት ሽህ አመታት በፊት ነዉ ።በጊዜው በቀይባህር አቋርጦ በሚሄደው የሲራራ ንግድ ወርቅና ማዕድንና ይገበያዩ ነበር ። ከዘመናት በኋላም በተለያዩ መንገዶች አንዳቸው ለአንዳቸው በመድረስ ታሪክ ተጋርተዋል ። ስለዚህም የሁለቱ መሪዎች መገናኘት አዲስ ጓደኝነት ሳይሆን የኖረና የነበረውን ወዳጅነት ማስቀጠል ነዉ ።
.......

ጋዜጠኛዋ ቀጥላለች እኔ ግን ፅሁፉ እንዳይረዝም ይህቺን ስለ ጥንታዊነቷ ስልጡንነቷ ታላቅነቷ ሀያልነቷ በተዋበ ቃላት ያሽሞነሞነችዉን ጋዜጠኛ ከወገቤ ጎንበስ ብዬ ምስጋናዬን በመግለፅ በዚህ ላብቃ ።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.