በህንድ 187 ሰዎች ለሚፈለጉበት የስራ ዘርፍ 8,000 ሰዎች ለስራ ፈተና መቀመጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል
#ethiopia |×በህንድ ኦዲሻ ግዛት ለፖሊስ ድጋፍ ለሚሰጡ የፀጥታ ኃይሎች 187 ሰዎች ብቻ ቢፈለጉም 8,000 ያህል ሰዎች ለፈተና ተቀምጠዋል።
ፈተናው በአውሮፕላን መንደርደሪያ አስፋልት ላይ የተሰጠ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተፈታኞች በጣም መብዛታቸው ነው ተብሏል።
ፈተናው በክፍት ቦታው ላይ ሲሰጥም ተፈታኞችን ለመቆጣጠር ድሮን ጥቅም ላይ ውሏል።
ለፈተናው ከ10,000 በላይ ሰዎች መመዝገባቸው ሲነገር በፈተናው እለት የተገኙት 8,000 ያህሉ ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳን ለስራው ብቁ ለመሆን አምስተኛ ክፍልን መጨረስ በቂ ነው ቢባልም በርከት ያሉ የመጀመሪያ እና ከዛ በኋላ ያሉ ድግሪዎች ያሏቸው ሰዎች መመዝገብ እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ሆነው 18 በመቶ ያህሉ ስራ አጥ በሆነባት ህንድ ስራ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። #tm
10 months ago