ግንኙነታችሁ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ ከትዳር አጋራችሁ እነዚህን 5 ነገሮች መጠየቅ አቁሙ
ብዙ ሰዎች አጋሮቻቸው የፈለጉትን ያህል ፍላጎታቸውን ስላማያሟሉላቸው ብስጭት ይሰማቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን፣ እያንዳንዱ አጋር የማይጨበጡ ፍላጎቶችን መተው ሲችል የፍቅር ግንኙነቱ ይበልጥ ቀላል ይሆናል።
Your Tango ላይ እንፈሰፈረው ፣ አጋሮች በትዳራቸው ወይም በፍቅር ግንኙነታቸው ውስጥ ሁሌ ሊጠይቋቸው የማይገቡ አንዳንድ ነገሮች እኝህ ናቸው;
1. ሁልጊዜ ሃሳብን እንዲረዱ መጠበቅ
በግንኙነቶች ውስጥ ለግጭት መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ፣ አጋርዎ ሳይነገረው ሁልጊዜ ውስጣችሁን እንዲረዳ መጠበቅ ነው። እንዲያውም፣ በግልጽ መነጋገር በውል ካልታወቁ ምልክቶች (codes) የበለጠ ውጤታማ ነው። የሚሰማዎትን በግልጽ መናገር ሲጀምሩ፣ "አልተረዳሁም" በሚል የሚመጣው ብስጭት ይቀንሳል።
2. አጋርዎን ለመለወጥ መሞከር
አስከፊ ጉዳት የሌለውን የአጋርዎን ስብዕና ወይም ልምዶች ለመለወጥ መሞከር በጣም አድካሚ ነው። በተጨማሪም፣ ይህ ድርጊት አጋርዎ አክብሮት እንደሌሎት ሊያደርግ ይችላል። አጋርዎ እርስዎ በሚፈልጉት መንገድ እንዲለወጥ ከመገፋፋት ይልቅ፣ መቀበልን ይለማመዱ።
3. ብቸኛው የደስታ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ
አጋርዎ እርስዎን ደስተኛ የሚያደርግ ብቸኛው ሰው እንዲሆን መጠበቅ በራስዎም ሆነ በግንኙነቱ ላይ ሸክም ይፈጥራል። እያንዳንዱ ሰው ከትዳር አጋሩ ውጪ እንደ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ያሉ የግል ነጻነቶች ሲኖሩት የፍቅር ግንኙነቱ ይበልጥ ጤናማ ይሆናል።
አጋርዎ የደስታዎ ማሟያ እንጂ ብቸኛው የደስታዎ ምክንያት መሆን እንደሌለበት ያስቡ።
4. እንደ የፍቅር ታሪኮች (ፊልሞች) እንዲሆኑ መጠበቅ
የፍቅር ታሪኮች ብዙውን ጊዜ እውነታዊ ያልሆኑ ክስተቶችን ያሳያሉ፤ በእውነተኛ ህይወት ግን ነገሮች እንደዛ ላይሆኑ ይችላሉ። ዘላቂ ግንኙነት የሚገነባው ከአጋርዎ የሚመጡ ትንንሽ ነገሮችንም ጭምር በመቀበል እና በማድነቅ ነው።
5. አጋርዎ ሁልጊዜ በእርስዎ ሃሳብ እንዲስማማ መፈለግ
በግንኙነት ውስጥ የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ የተለመደ ነው። አጋርዎ በሁሉም ነገር ላይ እንዲስማማዎት ሁልጊዜ አያስገድዱ። ግንኙነቱ ጤናማ እንዲሆን የአጋርዎ አመለካከት ምንም ይሁን ምን ማክበርን ይማሩ።
የማይጨበጡ ነገሮችን መጠየቅ በማቆም፣ አጋርዎ በቅንነት እንዲወድዎት ዕድል ይሰጡታል።

10 months ago