Logo
Getu Temesgen
ሲንጋፖር አጭበርባሪዎችን በግርፋት ልትቀጣ ነው
#ethiopia | ሲንጋፖር ከመጪው የፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ አጭበርባሪዎችን በ24 ግርፋት እንደምትቀጣ አስታወቀች።

ሲንጋፖር የማጭበርበር ተግባራት እየበዙ ነው ያለች ሲሆን አጭበርባሪዎች ከሚቀጡት የገንዘብ መቀጮ እና እስራት በተጨማሪ 1.2 ሴንቲሜትር ውፍረት ባለው መግረፊያ እርቃናቸውን ሆነው 24 ጊዜ እንደሚገረፉ አስታውቃለች።

የግርፋት ቅጣት በሲንጋፖር የተለመደ ሲሆን ከ50 አመት በታች የሆኑ ወንዶች በስርቆትና ወሲባዊ ጥቃት ጥፋተኛ ሲባሉ ይቀጣሉ።

ሲንጋፖር በማጭበርበር ተግባራት ወቅት ገንዘቡ እንዲሸሽ የሚተባበሩ በ12 ግርፋት ይቀጣሉ ብላለች።

ሲንጋፖር ከ2020-2025 ከተፈፀሙ ወንጀሎች መካከል 60 በመቶው ከማጭበርበር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ስትገልፅ በዚሁ ጊዜ 2.8 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ያደረሱ 190,000 የማጭበርበር ተግባራትም መፈፀማቸውን ገልፃለች።

ከሚፈፀሙት የማጭበርበር ተግባራት መካከል ሃሰተኛ ሊንኮች፣ ሃሰተኛ ስራዎች ፣ ሃሰተኛ ኢንቨስትመንቶችና ሌሎች ሰዎችን መስሎ ማታለል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
#tm

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.