Logo
Getu Temesgen
ላይት ኢንቨስትመንት ከፈረሰኞቹ ጋር አዲስ አጋርነት መሰረተ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ፈርቀዳጅ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ (ፈረሰኞቹ) ከላይት ኢንቨስትመንትስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኃይል ሰጪ መጠጥ ድርጅት ጋር ቢሾፍቱ በሚገኘው የክለቡ አካዳሚ ስምምነታቸውን በፊርማ አረጋግጠዋል።

ይህ ስምምነት ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን በዋናነት ክለቡ ለሚያደርጋቸው ውድድሮች እና ልምምዶች የሚያስፈልገውን የኃይል ሰጪ መጠጥ አቅርቦት ላይ ያተኮረ እና፣ ለተጫዋቾቹ ብቃት መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል።

ድርጅቱ ለክለቡ ተጫዋቾች እና የቴክኒክ ቡድን አባላት በቂ የኃይል ሰጪ መጠጥ በቋሚነት ያቀርባል የተባለ ሲሆን በምላሹም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላይት ኢንቨስትመንት ኃ.የተ.የግ.ማህበርን ይፋዊ የኋይል ሰጪ አቅራቢ አድርግ ተቀብሏል።

መጠጡ ተጫዋቾች በጨዋታ ወቅት የሚያጡትን ኃይል በፍጥነት እንዲተኩ እና የትኩረት አቅማቸው እንዲጨምር ለማገዝ ታስቦ የቀረበ ነው።

የክለቡ አመራሮች በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ እንዲህ ያሉ ትብብሮች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት እና ለክለቦች አቅም መጎልበት ወሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን "ተጫዋቾቻችን በሜዳ ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ዘመናዊ የአቅርቦት ስርዓት መዘርጋት አለብን፤ ይህ ስምምነትም የዚሁ አካል ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የኃይል ሰጪ መጠጥ አምራች ድርጅቱ በበኩሉ፣ በኢትዮጵያ ትልቅ ስም ካለው እና በርካታ ደጋፊ ካለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር መስራት ምርቱን ለተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጿል።

ይህ አዲስ ጥምረት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ያሉ ሌሎች ክለቦችም መሰል ትብብሮች እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።

የላይት ኢንቨስትመንት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የሚያመርተው የኋይል ሰጪ ኤሌክትሮ ላይት በውስጡ የቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ቢ እንዲሁም ግሉኮስን የያዘ ተበጥብጦ የሚጠጣ ሃይል ሰጪ ነው።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.