በብራዚል አንዲት እናት የወሊድ መከላከያ ተጠቅማ እያለች አስገራሚ ህፃን ተወለደ
#ethiopia | በብራዚል ጎያስ ግዛት ውስጥ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ለየት ያለና ዓለምን ያስገረመ ክስተት አስተናግዷል።
ማቴዎስ ገብርኤል የተባለ አዲስ የተወለደ ህፃን፣ እናቱ እርግዝናን ለመከላከል በማህፀኗ ውስጥ አኑራው የነበረውን "አይዩዲ" (IUD) የተሰኘ የወሊድ መከላከያ በትንሽ እጁ ጨብጦ መወለዱ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
የህፃኑ እናት ኩይዲ አራውጆ ዲ ኦሊቬራ፣ መከላከያውን (IUD) ለሁለት ዓመታት ያህል ስትጠቀም የቆየች ቢሆንም፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ ማርገዟን አውቃለች።
በወቅቱ ሀኪሞች መከላከያውን ለማውጣት መሞከር በእርግዝናው ላይ አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል ሳይወጣ እንዲቆይ ወስነው ነበር። ይሁን እንጂ ህፃኑ ሲወለድ መከላከያውን በእጁ ይዞ መውጣቱ የህክምና ባለሙያዎችን ጭምር አስደምሟል።
በኔሮፖሊስ የሚገኘው የሳግራዶ ኮራሳው ዲ ጀሱስ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ ምንም እንኳን እንዲህ ያሉ የወሊድ መከላከያዎች እስከ 99 በመቶ አስተማማኝ ቢሆኑም፣ አልፎ አልፎ መከላከያው ካለበት ቦታ ሲንቀሳቀስ እርግዝና ሊከሰት እንደሚችል ገልጸዋል።
ህፃኑ መከላከያውን ይዞ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት የተሰራጨ ሲሆን፣ ብዙዎች "ታጋይ ህፃን" እና "አሸናፊ" በሚሉ ስሞች እየጠሩት ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት እናትየውና ህፃኑ ማቴዎስ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። ይህ ክስተት ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ መቶ በመቶ አስተማማኝ ላይሆን እንደሚችል ትልቅ ማሳያ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
#menaharia_fm

10 months ago