Logo
Getu Temesgen
ህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

📍 የአብነት ትምህርት ቤቶችን በቀጣይ ይገነባል !
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ለገሂዳ ወረዳ የሚገኘው የሸክፍ (ወጅሮ/ችኮሜዳ) ደብረ ፀሐይ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በአዲስ አበባ ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተካሂዷል።

የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበርና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ቀሲስ መርጌታ ተመስገን ከፍያለው በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ ግንባታውን ለማካሄድ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸው ከዚህም መካከል በአዲስ አበባና በደሴ ከተማዎች የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ማቋቋም፣ የቤተ ክርስቲያኑን ፕላን ማዘጋጀት፣ በቤተ ክርስቲያኑ ስም የባንክ ሂሳብ ቁጥር መክፈት እንዲሁም ለህንፃው ሥራ የሚያስፈልገውን አጠቃላይ የዋጋ ግምት 14 ሚሊዮን ብር (አስራ አራት ሚሊዮን ብር) የማውጣት ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

እስካሁን በተከናወነው ሂደትም አነስተኛ ገቢ የማሰባሰብ ሥራ በመሰራት፣ የግዢ ኮሚቴ በማቋቋም የግዥ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ለግንባታ የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች የማቅረብ ስራና የህንፃ ቤተ ክርስቲያኑን የማስጀመር ሥራ ተከናውኗል። ህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ዓመት ከአምስት ወር ሆኖት አሁን ከህንፃው ሥራ መሰረት ከማውጣት ጀምሮ እስከ ኮለን የማውጣት ድረስ እየተሠራ ይገኛል።

በተጨማሪም በቦታው ላይ በአካል በመገኘት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ፣ ነባሩን ቤተ ክርስቲያን ከነበረበት ቦታ እንዲነሳ በማድረግ በምትኩ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን የመሥራት፣ ቦታውን በማሽንና በሰው ጉልበት የማፅዳት፣ በምህንድስና የቅየሳ ሥራ እንዲሠራ የማድረግ እንዲሁም ዙሪያውን የማስገንባትና የሙሊት ሥራ መሠራቱ ገልጸው በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ የአብነት ትምህርት ቤቶች ለመገንባት እቅድ መያዙን ቀሲስ መርጌታ ተመስገን ከፍያለው ገልጸዋል።

ህንጻ ቤተክርስቲያኑን ለማጠናቀቅ በመላው አለም የሚገኙ የእምነቱ ተከታይ በጉልበት በሀሳብ በገንዘብ በቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርግ ገልጸዋል።

ቤተክርስቲያኑ ግንባታ ለማገዝ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000457762449 ክፍት መሆኑን ኮሚቴው አሳውቋል።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.