በአዲስ አበባ ከተማ 25 የትራፊክ ፍሰት ችግር ያለባቸዉ መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና መጋጠሚያዎች ተለዩ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ችግር ባለባቸዉ 25 መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና ማጋጠሚያዎች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።
በከተማዋ በተለይም በስራ መግቢያና መዉጪያ ሰዓት የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ፍሰትን መሠረት ያደረገ ስምሪት በመስጠት ጠንከር ያለ የማስተባበር ስራ እያከናወነ መሆኑን በባለስልጣን መስሪያቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌዉ ኢቲሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
የትራፊክ ፍሰት ችግር አለባቸው ብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች መካከል በለሚኩራ ክፍለከተማ በተለምዶ 72 ፣ሲኤምሲ መሪ ሳይት እና አያት መሪ ፣በአቃቂ ቃሊቲ ቶታል ማደያ እስከ አደባባይ እና ከማሰልጠኛ አቦ መብራት እንደሚገኙበት ተገልጿል ።
በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ከላምበረት እስከ ዲያስፖራ አደባባይ እና ከጉርድ ሾላ እስከ መገናኛ ተርሚናል ፣በኮልፌ ክፍለ ከተማ ከዘነበወርቅ እስከ ቶታል እና ከካራ እስከ አየር ጤና ፣በቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል እስከ ጊዮርጊስ መብራት ፣ከኤድናሞል አዉራሪስ ጉላጉል 22 እና በሌሎችም አከባቢዎች የትራፊክ ፍሰቱን የማስተካከል ስራ ተጠናክሮ ቀጥላል ተብሏል ።
በቀጣይ በጥናት ላይ በመመስረት የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ፍሰት ማስተካከል የሚያስችሉ የምህንድስና ማሻሻያዎች ስራዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ጨምረዉ ተናግረዋል ያለው ብስራት ኤፍ ኤም ነው።

10 months ago