Logo
YenetaTube
የዓለም ማዕከላዊ ቦታ በሆነቸው ኢየሩሳሌም በጎልጎታ ተራራ ላይ የሚገኘዉ የዴር- ሱልጣን ገዳም ያለው የኢትዮጵያ ይዞታ ክርክር አሁንም መቋጫ አላገኘም ተባለ

የጎልጎታ ባለይዞታዎች የስድስት ሃገራት አብያተ ክርስትያናት ናቸዉ። ከስድስቱ መካከል አንደኛዉ እኛ ነን። የጎልጎታ አባል የጎልጎታ ባለይዞታዎች ነን ይላሉ የገዳማቱ የሒሳብ ክፍል ሐላፊ መላከሰሌም አባ ገ/ኪዳን፡፡

ከስድስቱ መካከል ሦስቱ ታላላቆች ግሪክ፤ ላቲን እና አርመን ሲሆኑ ፤ መለስተኛ አብያተ ክርስትያናት ተብለዉ የሚመደቡት ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ- ክርስትያን ፤ የግብጽና የሶርያ ናቸዉ። የጎልጎታ ቀራንዮ በእነዚህ በስድስቱ የተያዘ ነዉ።

ገዳሙ ከንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ርስት ሆኖ መቆየቱ ሲገለገሉበት መቆየታቸው ይነገራል ፡፡ይሆን እንጂ አሁንም ድረስ ይህ ጥንታዊ ፤ ታሪካዊ ስፍራ በሌሎች ሊነጠቅ የሚችልበት ሆኔታ እንዳለ ስጋታቸውን ይናገራሉ እኚህ አባት ፡፡

በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በዴር ሱልጣን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ ጥረት ያላደረገ ያልደከመ እንዴሌለ ይናገራሉ፡፡

በቅርቡ እንኳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር ) በእስራኤል በነበራቸው ቆይታ ስፍራው ድረስ በመሄድ ከአባቶች ጋር መመከራቸውን እና ከእስራኤሉ አቻቸው ጋርም በጉዳዩ ላይ መምከራቸውን ተናገረዋል፡፡

በስፍራው ያሉ መነኩሳት ያሉባቸውን ችግሮችም ለመቅርፍ ሰፊ ጥረት የተደረገ ቢሆንም 200 መቶ አመታት ሲንከባለል የቆየ በመሆኑ በሚፈለገው ልክ ምላሽ ማግኘት እንደልተቻለ ገልጸዋል፡፡

በእስራኤል (ባለበት ይቆይ የሚባል ህግ አለ በጎለጎታ ያሉት የኢትዮጲያ ቤክርስቲያናት (መድኋኒአለም እና ሚካኤል ) እየተገለገለችባቸው ትገኛለች ፡፡ግብጹችም ስፍራውን አልወሰዱም እኛም አገልግሎቱን አላቋረጥንም ፡፡መነኩሳቱ ያሉባቸውን የመብራት ፤የውሃ የማዘጋጀበታዊ አገልግሎቱችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ከጥቁር ሕዝብ መካከል በእስራኤል ይዞታ ያላት ኢትዮጲያ መሆኗን የሚመሰክሩት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራም ንጉሤ ይህ ይዞታ በጎልጎታ ተራራ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀድሞ ጊዜ ነገሥታቱ እና መኳንንቱ የሰሩት ብዙ ሕንፃና ንብረት እንዳለ አንስተው፡፡የእስራኤል መንግስት በተለያዩ ጊዜት ለአቤተክርስቲያናቱ ድጋፍ እና ጥገና እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የእስራኤል ምክር ቤት አባል ጸጋ ፋንታሁን (ዶ/ር)በበኩላቸው በእስራኤል በኩል ችግሮን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የሚመለከታቸው አባቶችን በሰአቱ ማግኘት ባለመቻላችን ችግሮ መቁየቱን አንስተዋል፡፡

የርስቱ ባለቤት ነኝ የምትለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ጉዳይ ለመፍታት አንድም ጊዜ ጫና አድርጋ አታውቅም ተብላ ተወቀሳለች።

ርስቱ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚወክል ሀብት ሆኖ ሳለ ይህንን ሀብት እንደሀገራዊ ሀብት ለማስከበር መንግሥትም ጠንከር ያለ ጫና ሊያደርግ ይገባዋል ተብሏል ።

Ethio Fm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.