Logo
Getu Temesgen
በሃዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ
#ethiopia | ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል።

ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በዚህም ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ ሰዎች በየእለቱ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5ቀን እስከ ህዳር 17ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ሌሎች ሃገራት ላይ ተሞክሮ ለውጥ ያመጣ ዶሚድስፔር የተባለ ፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገር ቤት በማስገባት ለ16 የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በህክምና ላይ ላሉት 5 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሰጥተናል ብለዋል።

መድሃኑቱ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መቅደስ በህክምና ላይ ያሉት 5ቱ ተጠቂዎች የማገገም ሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በፅኑ ህሙማን ክፍል 1ታማሚ እንዳለ የተነገረ ሲሆን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.