Logo
FastMereja

ሰባት ነፍሳት እና ዐሥራ አምስት ሚሊዬን ብር
============================
ህዳር 5 እና 6 /2018 ለሀራንጃ መድኃኔዓለም የቀጥታ ሥርጭት ሲዳማ ሐዋሳ ላይ የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ ሲደረግ መቆየቱ ይታወቃል።

በመርሐግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ከኮሚቴው በተነገረው መግለጫ መሠረት ከ 15,000,000.00 (ከዐሥራ አምስት ሚሊዬን ብር በላይ መሰብሰቡ ተነግሯል። ከዚኽ በተጨማሪ ሰባት የቤተሰብ አባላት ከፕሮቴስታንት እምነት ወደ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መምጣታቸውን በቀጥታ ሥርጭቱ ተመልክተናል።

ይኽንን መርሐግብር ከኮሚቴው ጋር በመተባበር ያስተባበረው ሎዛ ኹነትች መኾኑ ተሰምቷል።
ኮሚቴው አጽንዖት ሰጥቶ ባሳሰበው መሠረት ከግማሽ በላይ የሚኾነው ገንዘብ ወደ አካውንቱ የገባ ስላልኾነና ቃል የተገባ ስለኾነ ቃል የገቡ በሙሉ በተቻላቸው ፍጥነት ቶሎ አስገብተው ቤተክርስቲያኑ እንዲጠናቀቅ የሚችሉትን ኹሉ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የሀራንጃ መድኃኔዓለም ታሪክ

የአረንጃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘው በሲዳማ ሀ/ስብከት በሸበዲኖና ቦርቻ ወረዳ ቤተክነት ከሀዋሳ ከተማ በ48ኪ ሜ ርቀት ላይ የሚገኝና ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነው::

የመድኃኔዓለም ታቦተ ህጉ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት በደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በ1874 ዓ ም በሲዳማ ክልል ከበሌላ ከተማ በ4 ኪ ሜ ርቀት ላይ ኢቲሳ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማህበር አነስተኛ መቃኖ በመስራት ታቦቱን አስገቡት። ሆኖግን ቦታው አመቺ ካለመሆኑ የተነሳ በድጋሚ በአረንጃ ቀበሌ አዲስ መቃኞ ቤት ሰርተው በ1876 ዓ ም ራስ ባልቻ አባ ነፍሶ ከአከባቢው ሀገር ሽማግሌዎችና ምዕመናን ጋር በአጀብና በሆታ በእልልታ አስገቡ። አሁን በቤተክርስቲያኑ በስጦታ ከራስ ባልቻ አባ ነፍሶ የተበረከተ የብርና የነሀስ መስቀሎች መጎናፀፊያዎች የብራና መጽሐፌት ይገኛሉ።

ከእነዚህም መካከል ወደ እንግሊዝ የተወሰደ አንድ የብራና መጽሐፍ በቦታው ተወላጅ የሆነች አንዲት እህት በሙዚየም ውስጥ ለጉብኝት በገባችበት ወቅት ይህን መጽሐፍ ተመልክታ ስታነበው ከኢቲሳ የመጣ የሚል ጽሑፍ ተመልክታ ይሄማ የአገሬ የመድሃኒአለም መፅሀፍ ነው ብላ ተከራክራ ተፃፅፋ ልታስመልስ ችላለች አሁን በዚህ ይገኛል ።

ቤተክርስቲያኑ አሁን ላይ 144ዓመት ያስቆጠረና ብዙ ገቢረ ታዕምራት የሚደረግበት ቦታ ነው የአከባቢው ምዕመን የለ ዕምነት ልዮነት እሚጠብቁትና እሚማፀኑት ዝናብ ቢዘገይባቸው በህብረት በቦታው ተማፅነው ዝናብ እሚያገኙበት ቦታ ነው ከዚህም የተነሳ የአከባቢው ምዕመን ያለ ሀይማኖት ልዩነት የመድኃኔዓለም አባታችንን ስም እንዃ ከፍቅራቸው የተነሳ መድዬ ብለው ነው የሚጠሩት።

ከተለያዮ ዓለማት መጥተው ብዙ የተደረገላቸው ምዕመናን በምስክርነታቸው ሲደመጡ ተሰምቷል ።
እኛም የዚህ ታላቅ በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ ቤተክርስቲያኗ ጥሪዋን ለልጆቿ ታስተላልፋለች።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።አሜን።

ቤተክርስቲያኑን ለመርዳት
ንግድ ባንክ_ 1000726667188
አቢሲንያ _241419592
አዋሽ _013521676947200

የውጪ አካውንት
$2407818533
Zel=+1 2407818523

ስልኮች
0916583334
0911369366
0927067797
0913107659
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.