በይርጋለም የ12 ዓመት ህጻን ልጅ የደፈሩት የ65 ዓመት የኤች አይቪ ታማሚ የ23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው
በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የይርጋለም ከተማ አስተዳደር የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው የ65 ዓመት ግለሰብ የ23 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደግነት ደስታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ፥ የከተማው ነዋሪ የሆነ አቶ ናስር ኑር የተባለ የ65 ዓመት ግለሰብ ነሐሴ 6/12/2017 ዓ.ም በከተማው 06 ቀበሌ የ12 አመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት መፈጸሙን የሚገለፅ መረጃ ለፖሊስ ይመጣል።
ፖሊስም ጉዳዩን ከፍትህ መዋቅር ጋር በመመርመር በሰውና በህክምና ማስረጃ በማጣራት ለከተማው ዐቃቤ ህግ አስተላልፏል።
በምርመራና መረጃ በማሰባሰብ ሂደትም ግለሰቡ ይህን አስነዋሪ ድርጊት ከመፈፀሙ ባሻገር የኤችአይቪ /ኤድስ (HIV/AIDS) ታማሚና እንደሆነና እራሱን አውቆ የመድሐኒት ተጠቃሚ እንደነበር ማወቅ መቻሉን አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ጉዳዩን የያዘዉ የይርጋለም ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ሲያጣራ የቆየው የከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሹን " ጥፋተኛ ነህ " በማለት ተከሳሹ እንዲከላከል ቢጠይቅም መከላከል አልቻለም።
እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚ መሆኑን እያወቀ በታዳጊዋ ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ጥፋቱን በማክበድ በቀን 4/2/2018 በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹን በ23 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
seledadotio

12 months ago