Logo
Getu Temesgen
"ሁዋሶንግ-20" አስፈሪው የሰሜን ኮሪያ ባሊስቲክ ሚሳዔል
#ethiopia | ሰሜን ኮሪያ በ80ኛ ዓመቱ የሰራተኞች ፓርቲ ምስረታ በዓል ላይ እጅግ ኃይለኛ የተባለውን አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳዔል ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገች፡፡

ሁዋሶንግ -20 አይ ሲ ቢ ኤምን በወታደራዊ ትዕይንቱ ላይ ያስመለከቱት ኪም ጆንግ ኡን በኩራት አስመልክተውታልም ተብሏል ፡፡

እጅጉን አውዳሚውን የጦር መሳሪያ ለዓለም ማስተዋወቃቸው ተሰምቷል ኪም ጆንግ ኡን፡፡

የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ወኪል ኪም ጆንግ ኡን ባሊስቲክ ሚሳዔሉን በወታዳራዊ ትዕይንቱ ላይ ተመልክተውታል ፤ሁዋሲንግ-20 በሄራዊ ኩራት ነውም ሲልም ዘግቧል ፡፡

ፒዮንግያንግ ሁዋሶንግ-20 ባሊስቲክ ሚሳዔልን ይፋ ስታደርግ በዓለም አደባባይ ላይ ወታደራዊ ጡንቻዬን ዕወቁልኝ ስትል ነው በሚልም ምዕራቡ ዓለም ተችቷታል ፡፡

ሁዋሶንግ -20 በአሁኑ ሰዓት ሰሜን ኮሪያ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስርዓት አቅሟ ምን ላይ እንደደረሰ እንዲሁም ፍላጎቷን የሚያሳይ ነው ፡፡

ተከታታይ የሁዋሶንግ ባሊስቲክ ሚሳዔል ምርት ላይ ያተኮረችው የኪሞቹ አገር አህጉር አቋርጦ ማውደም የሚችል የጦር መሳሪያ ስርዓት ባለቤት መሆኗን የሚጠቁም አድርጎላታል ፡፡

ሁዋሶንግ-20 በርካታ የኑክሌር አረር ጫፎችን በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሸከም ተደርጎ የተሰራ ሳይሆን አይቀርም በሚልም ወታደራዊ አዋቂዎች ሀሳባቸውን በማጋራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሁዋሶንግ-18ን ቀደም ሲል ፒዮንግያንግ ማምረቷም የሚዘነጋ አይደለም ፡፡NBC

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.