Logo
YenetaTube
በሀገረ አሜሪካ ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በላይ የኖሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ኤርሚያስ መኮንን ደራሲ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ናቸው፡፡ አቶ ኤርሚያስ የሕዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከመቀመጡ ከስድሰት ዓመት በፊት፣በአባይ ወንዝ ዙሪያ የተፈጠረባቸውን ሀገራዊ ቁጭት ተንተርሰው “የጽናት ናሙና” በሚል ርዕስ የከተቡትን ጥበባዊ ሥራ፣ ለሕትመት ብርሃን ማብቃታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይኽ ዘመን ተሻጋሪ ሕልምን የሰነቀ መጽሐፍ፣ ኀሙስ መስከረም 22 2018 ዓ.ም(October 2, 2025) በሒልተን ሆቴል፣ከቀኑ 8፡00 ሰዐት በይፋ ይመረቃል፡፡
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲ፣ ሕዳሴው ግድብ ከጥንስሱ ጀምሮ እሰከ መቋጫው ባለፈባቸው ፈታኝ ዓመታት ውስጥ የድርሻቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡በተለይም፤ በውጪ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በማነሳሳት፣ በርካታ የቦንድ ሽያጭ እንዲካሄድ፣ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፤ ከዚኽም በተጨማሪ፣ በአፍሪቃ ሀገራት በመዘዋወር፣ የኢምባሲ እና ቆንስላ ጽ/ቤት ተወካዮችን በማስተባበር “የፐብሊክ ዲፕሎማሲ” ሥራ ሠርተዋል፡፡ ይኽም አበርክቷቸው ከግምት ተጥፎ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸኋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ፣በሀገር ፍቅር ስሜት ሲቃትቱለት የነበረው አባይ ወንዝ፣በከንቱ የሚፈስበት ዘመን አክትሞ ለፍሬ ሲበቃ በመመልከታቸው፣ ራሳቸውን “ሕልሙ እንደተሳካለት ዕድለኛ ደራሲ” ነው፤የሚቆጥሩት፡፡
በአቶ ኤርሚያስ መኮንን የመጽሐፍ ምርቃት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም፤ ይህ ወቅታዊ እና ታሪካዊ የመጽሐፍ ምረቃት ሥነሥርዓትን የሚዘግቡልንን ባለሙያዎች እንድትመድብሉን እየጠየቅን፣ ለሚደረግልን ትብብር በቅድሚያ እናመስግናለን፡፡

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.