Logo
Getu Temesgen

የሃዋይ ኪላዌያ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ፡ ላቫ እስከ 1,300 ጫማ ከፍታ ተተኮሰ! 🌋🔥
#ethiopia | በአሜሪካ ሃዋይ ግዛት የሚገኘው ታዋቂው እና ንቁ የእሳተ ገሞራ ስፍራ የሆነው ኪላዌያ (Kīlauea) እሳተ ገሞራ መፈንዳቱ ተዘገበ።

ይህ 'ክፍል 34' (Episode 34) የተሰኘው ፍንዳታ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከሁለት የተለያዩ መውጫዎች (vents) ላቫን በአየር ላይ ተኩሷል።

የዩኤስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ከመውጫዎቹ አንዱ የሆነው ሰሜናዊው መውጫ ላቫን እስከ 330 ጫማ (100 ሜትር) ከፍታ ሲያወጣ፣ ሌላኛው የሆነው ደቡባዊው መውጫ ደግሞ ከፍተኛውን ሪከርድ በመስበር እስከ 1,300 ጫማ (400 ሜትር) የሚደርስ ግለት ያለው ላቫ ወደ ሰማይ ማስወንጨፍ ችሏል።

ይህ አስደናቂ የተፈጥሮ ክስተት ለበርካታ ሰዓታት የዘለቀ ሲሆን፣ የላቫ ፍሰቱ በሙሉ በሃሌማኡማኡ (Halemaʻumaʻu) እሳተ ገሞራ አፍ (ክሬተር) ውስጥ የተገደበ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ፣ ፍንዳታው ከፍተኛ መጠን ያለው የእሳተ ገሞራ ጋዝ (Volcanic Gas) ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተጠቁሟል።#menaharia_fm
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.