ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የህፃና ት/ቤት በቤተ ጉራጌ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ
(ይትባረክ ዋለልኘ)
• የኢትዮጽያዊያን የመፅሐፍ እና የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲያደርግላቸዉ ጠይቀዋል
#ethiopia | የአንጋፋው ኢትዮጵያዊው ምሁር ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ በህይወት በነበረበት ወቅት ለሐገርና ለሕዝብ ይጠቅማል ከሚላቸዉ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ትምህርት እና ለንባብ እንደሆነ የራሱን የህይወት ልምድ ጠቅሶ ይናገር ነበር። በመሆኑም ይህን ምሁር በስራዎቹ ለማሰብና ለማስታወስ ይረዳ ዘንድ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ጓደኞቹ በሁሉም የሐገሪቱ ክልሎች ለሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በስሙ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ በመገንባትና በማደራጀት ለህዝብ አገልግሎት እንዲዉል ለማድረግ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ከዚህ ዓለም የተለየበትን አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የመታሰቢያ ስራዎች ሲሰሩ ሲቆይተዋል ።
የዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም አንዱ አካል የሆነዉ በማዕከላዊ ኢትዬጽያ ክልል ጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ የፈረዝየ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ልዩ ቦታ አንዛናባጥ የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ የቅርብ ጓደኛ በሆነዉ በአቶ ሚኪያስ ተሬሳ የተገነባዉ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የህፃና ት/ቤት መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም የአካባቢዉ ህብረተሰብ በተገኙበት ለህፃናት የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና ለቤተመፅሐፍቱ በርካታ መፅሐፍትን በስጦታ በማበርከት በይፋ ተመርቋል። በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ የእምድብር የፈረዝየ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የአካባቢ የሐገር ሽማግሌዎች ወጣቶች የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል::ነዋሪዎችም በአካባቢያቸው ይህን አይነት ለትውልዱ የሚተርፍ ታላቅ ስራ በመሰራቱ እጅግ መደሰታቸውን የገለፁ ሶሆን ይህን ታላቅ ስራ ለፈፀሙ ኢትዮጽያዊያን በአካባቢው ባህል መሰረት በሶስት የሐገር ሾማግሌዎች ምርቃት አድርገዋል።
የመጀመሪያዉን “የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የቅድመ መደበኛ የህፃና ት/ቤት”ን የምርቃት ፕሮግራም ላይ ግንባታዉን ያደረገዉ አቶ ሚኪያስ ተሬሳ ጨሞሮ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የመታሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጆች የሆኑት አቶ በፍቃዱ ቸርነት፣ ሠዓሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል፣አቶ ሲሳይ ተፈራ፣እና እኔ ይትባረክ ዋለልኘ በቦታዉ ተገኘተን የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የህፃና ት/ቤትን መርቀን አስከፍተናል።እንዲሁም የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ቤተሰቦችን ጨምሮ ከተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶ በስጦታ የሰበሰብናቸዉን ለህፃናቱ መማሪያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ( ጥቂት የህጻናት ወንበሮች፣4 ካርቶን ደብተር፣በመቶዎች የሚቇጠሩ እርሳስ፣ላዺስ እና እስክርቢቶዎች) እና ለቤተመፅሐፍቱ የሚሆኑ መፅሐፍትን በስጦታ አበርክተናል።በተጨማሪም ቤተመፅሐፍቱን እና ት/ቤቱን በኃላፊነት የሚያስተዳድሩ ስድስት በአካባቢው ነዋሪዎች የተመረጡ አንድ ኮሚቴ በመመስረት ሙሉ ንብረቶቹን ለእነዚሁ ኮሚቴዎች እንዲረከቡ እና እንዲያስተዳድሩ አድርገናል።
ይህን የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የቅድመ መደበኛ የህፃና ት/ቤት”ን እውን ለማድረግ ግንባታዉን በኃላፊነት ተከታትሎ ያሰራልን የአካባቢዉ ነዋሪዉን አቶ ጀማል ስባኒ ንስራነ እና የመፀሐፍ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጋችሁትን ሁሉ በጣም እናመሰግናለን። በተለይ ከምርቃቱ አንድ ሳምንት በፊት እቦታዉ ድረስ በመሄድ የመፅሐፍ ድጋፍ ያደረገዉ ከቤት እስከ ከተማ ፕሮግራም አዘጋጁ ማህደር። እንዲሁም ዋሊያ ቡክ፣እነሆ መፅሐፍ፣ጃፋር መፅሐፍ፣ሀሁ መፅሐፍ እና የሐብከ ብርሃኔን ከልብ እናመሰግናለን።
ይህ የመታሰቢያ ቤተመፅሐፍ እና የቅድመ መደበኛ የህፃና ት/ቤትም በተሟላ መልኩ በሙሉ አቅም ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ አሁንም ለህፃናቱ የመሚሪያና የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ለቤተመፅሐፉ ሼልፎች በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል::
በመሆኑም የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ወዳጆች ተማሪዎች አድናቂዎች እና ለንባብ ለህፃናት ትምህርት ግድ የሚላችሁ ኢትዮጽያዊያን ግለሰቦችና ድርጅቶች ሁሉ አንድም ሁለትም ሳትሉ አቅማችሁ በፈቀደዉ መጠን የመፅሐፍ ድጋፍ እንድታደርጉ በማክበር እንጠይቃለን።
በቀጣይነት በቅርቡ በሚመሰረተዉ”በዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ፋዉንዴሸን” አማካኘነት ደግሞ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በሁሉም ክልሎች የገጠር ቀበሌዎች ላይ ቤተመፅሐፍና የቅድመ መደበኛ የህፃና ት/ቤት በየአመቱ እንደሚከፈት የፋዉንዴሸኑ ጊዜያዊ ኮሚቴዎች እና ጓደኞቹ በዚህ ፕሮግራም ላይ ገልፀዋል።
ድጋፍ ማድረግ የምትሹ በዚህ ስልክ በመደወል እና በፁሑፍ yetbarekyahoo.com ኢሜይል መልዕክት በመላክ ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
+251 91 163 2945
+251910102299
( ጓደኞቹ)

1 year ago